Loading...

ተልእኮ

ልጆች በነፃነት የሚመራመሩበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ፍላጎታቸውን እንዲያውቁ እና መክሊታቸውን እንዲፈልጉ ማስቻል!

ልጆች ነጭ ወረቀት ሳይሆኑ በውስጣቸው እምቅ ሀይልን የያዙ ኩራዞች ናቸው፡፡ የሚያቀጣጥለው ሀይል ካገኘ እጅግ በጣም ብዙ ጥበቦችን፣ፈጠራዎችን ለዚች ዓለም የማበርከት ከፍተኛ ዓቅም አላቸው፡፡ይህም ትልቅ ዓቅም ማቀጣጠል የሚቻለው አስተማሪዎች፣ቤተሰቦች፣የትምህርት ቤቱ ምቹ ሁኔታ፣ማህበረሰብ እንዲሁም ሚዲያ አብሮ መስራት ሲቻል ነው፡፡ ይህንንም በመረዳት ፍቅር አስኳላ ደረጃቸውን የጠበቁ የራስን ግንዛቤ የሚያሳድጉ፣የግል ህይወታቸውን የተሻለ ማረግ የሚችሉበትን ስልጠናዎችን በመስጠት ህይወታቸው ምሳሌ የሚሆን፣በህይወታቸው እጅግ በጣም ደስተኛ የሆኑ፣ አስተማሪነታቸውን በፍቅር የሚወዱ የዘመኑ እንቁ አስተማሪዎችን በማፍራት ልጆቹን በነፃነት እንዲፈልጉ በፍቅር ያግዛሉ፡፡ ቤተሰቦች ራሳቸው መሪ የሆኑ፣ራሳቸውን የገዙ፣ልጆቻቸውን እንደራሳቸው መቀበል የሚችሉ፣ትልልቅ ህልሞች ያልዋቸው፣አገልጋይ እና ትልቅ ራዕይ ያላቸው እንዲሆኑ የስልጠና መድረኮችን በማመቻቸት፣የተለያዩ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት የተሻሉ ቤተሰቦችን በመፍጠር አርአያ የሆኑ ቤተሰቦችን እንዲኖሩ እና ልጆቻቸው መክሊታቸው እንዲፈልጉ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ቤተሰቦች ይሆናሉ፡፡